በሩብ አመቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸዉ ተገለጸ

You are currently viewing በሩብ አመቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸዉ ተገለጸ

AMN ጥቅምት 8/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሦስት ወራት የህዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ ያረጋገጡ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

ከንቲባ አዳነች በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ፣ በክረምቱ ወራት ማህበረሰቡ ላይ የኑሮ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ ተግባራትን በመለየት ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የኑሮ ውድነት ጫናን ከመቀነስ አኳያ የገበያ ማረጋጋት፣ምርት በብዛት እንዲገባ የማድረግ፣ ገበያ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ብልሽቶችን የመቆጣጠር እና የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል ያስቻሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የክረምት ወቅት ተጽዕኖ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች ላይ ጫና እንዳያሳድር ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ለህዝቡ ያለውን ወገንተኝነት በተግባር ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል።

የሀገር ባለውለታዎችን፣አቅመ ደካሞች እና ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመለየት በሰው ተኮር ስራዎች ከ2 ሺ 500 በላይ ቤቶችን ለመሥራት ታቅዶ ከዚያ በላይ መከናወኑን ገልጸዋል።

ሰላምን የማጽናት ስራዎችም በህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ተሣትፎ ውጤታማ በሆነ መንገድ መከናወን መቻሉን ጠቁመዋል።

በዓላት እሴታቸውን ጠብቀው በሰላማዊ መንገድ እንዲፈጸሙ ብሎም የህዝብ አብሮነት እንዲጠናከርባቸው መደረጉንም ጠቁመዋል።

አዲስ አበባ የኮንፈረንስ ቱሪዝም የስበት ማዕከል እንድትሆን በማድረግ በርካታ የሀገር እና ዓለም አቀፍ ኩነቶችን ማስተናገድ መቻሏንም ጠቁመዋል።

የህዝቡም የእንግዳ ተቀባይነት እሴት እንግዶች ዳግም አዲስ አበባን እንዲመርጡ ያደረገ ነውም ብለዋል።

በግምገማ መድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን አበይት ተግባራት የደረሱበት የአፈፃፀም ደረጃ እንደሚገመገም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል።

መድረኩ የተገኙ ውጤታማ አፈፃፀሞችን በማላቅና ቀጣይነትን በማረጋገጥ ብሎም የታዩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ አመርቂ ስራዎች እንደሚከናወኑም ጠቁመዋል።

ለሁለት ቀናት በሚከናወነው መድረክም የቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡበት መመላከቱን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review