ኢትዮጵያ እና እስያ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ አጋርነታቸዉን ለማጠናከር ተስማሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና እስያ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ አጋርነታቸዉን ለማጠናከር ተስማሙ

AMN ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና እስያ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ አጋርነታቸዉን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት አመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር አጃይ ቡሻን ፓንዲ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ አህመድ ሽዴ በዉይይቱ ወቅት እንደተናገሩት በማደግ ላይ ያሉ ሃገራትን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍ እና ከአየር ንብረት ጋር ተያይዘዉ የሚታዩ ጉዳዮችን ለመፍታት በፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review