ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በባሌ ዞን በነበረን የሁለተኛ ቀን ቆይታ የወልመል ወንዝ የመስኖ ልማት እና ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ጉብኝት ባሻገር ወደ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሀረና ክላስተር በመገኘት ምልከታ አድርገናል ብለዋል።
እነዚህ በግንባታ ላይ በባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያሉ ፕሮጀክቶች በሃረና ደን የሪራ ኢኮ ሎጅ እና ከባቢውን ብሎም የመመገብያ ስፍራዎችን፣ በእግር እና መኪና መንገዶች የቡና ሱቆችን፣ የምግብ አዳራሾችን እስከ ቱሉ ዲምቱ የከፍታ መወጣጫ ስፍራዎች የሚያካትቱ ናቸው።
እነዚህ የልማት ሥራዎች ዘላቂ የቱሪዝም ፕሮጀክቶች የአካባቢ የሥራ ፈጠራ ዕድልን የሚያሰፉ እና የጎብኝዎችን ዕድል የሚያሰፉ በመሆኑ በልዩ ምልከታ የሚታዩ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።