በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ውጤታማ አመራር የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ስራዎች እንዲከናወኑ ማስቻሉት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ውጤታማ አመራር የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ስራዎች እንዲከናወኑ ማስቻሉት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

AMN ጥቅምት 9/2018

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው ውጤታማ አመራር የህዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ስኬታማ ስራዎች እንዲከናወኑ ማስቻሉን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ በ2018 ሩብ በጀት ዓመት በፓርቲ እና በህዝብ ንቅናቄ ስራዎች ላይ ያተኮረ ግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የፓርቲው አመራሮች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ በየዘርፉ ያለው አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ፓርቲው ተግባራዊ ያደረገው ውጤታማ አመራር ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስኬታማ ስራዎች እንዲከናወኑ አስችሏል።

ትልልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች መመረቃቸውን ጠቅሰው፤ በሁሉም መስክ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል።

መደመርን ማዕከል በማድረግም የፓርቲው፣ የህዝቡና የግሉን ዘርፍ በማቀናጀት ያሉ ሀገራዊ አቅሞች ጥቅም ላይ እንዲውሉ መደረጉ ለስኬቱ መገኘት ከምክንያቶቹ መካከል መሆኑን ገልጸዋል።

ገቢር ነበብ አካሄድን በመከተል በየአካባቢው ያሉ ጸጋዎችንና ዕድሎችን መሰረት ያደረጉ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት አቶ አደም ፋራህ፤ ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር ባህል እየዳበረ መምጣቱንም ተናግረዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ነው ያመላከቱት።

በዛሬው የግምገማ መድረክም በጋራ የታቀዱ ጉዳዮች አፈጻጸም መገምገም እና ቀጣይ ስራዎች ርብርብ የሚጠይቁ ጉዳዮችን ለይቶ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

የግምገማ መድረኩ በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ የአፈጻጸም ወጥነት እንዲኖር ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review