ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በሚገኙ ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና አቅመ ደካማ እናቶች 6ሺህ ጫማዎችን ድጋፍ አደረጉ

You are currently viewing ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በሚገኙ ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና አቅመ ደካማ እናቶች 6ሺህ ጫማዎችን ድጋፍ አደረጉ

AMN ጥቅምት 9/2018

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በባሌ ዞን በነበራቸው ጉብኝት በዞኑ በሚገኙ ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እና አቅመ ደካማ እናቶች 6ሺህ ጫማዎችን ድጋፍ አድርገዋል።

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው አበይት ጉዳይዎች ውስጥ አንዱ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ሲሆን በትምህርት ዘርፉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን በመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

ይህንን ሚና በማጠናከር ላለፉት አምስት አመታት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች ጽ/ቤቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባት በተጨማሪ ለተገነቡት እና በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ት/ቤቶች እና ተማሪዎች ያለማቋረጥ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ ሲሆን የዛሬው ስጦታም የዚህ ሥራ አንዱ አካል መሆኑን ከጽ/ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review