ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ በሩብ ዓመቱ እና በ90 ቀናት ስራዎቻችን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የትኩረት መስኮች የተገኙ በርካታ አበረታች ዉጤቶችን ይበልጡን አጠናክሮ ለማስቀጠል ፣ የታዩ ጉድለቶችን ፣ ብልሹ አሰራሮችን በፍጥነት ለማረም እና ዉጤታማነትን በወጥነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።

በበጀት አመቱ ቀሪ ጊዜያት ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባሮቻችን ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

በዚህም የኑሮ ጫናን ለመቀነስ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርት አቅርቦት መሻሻሎችን ማስቀጠል ፣ የከተማዉን ሰላም ዘላቂ ማድረግ ፣ የገቢ አሰባሰባችንን ማሳደግ ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር የታየዉን ተስፋ ሰጪ ለዉጥ ይበልጡን ማስፋት፣ የስራ ዕድል ፈጠራን በማሳደግ የህዝባችንን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ይበልጡን አጠናክረን የምናስቀጥል ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review