የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ከሚገኘዉ የአለም ባንክ እና አይኤምኤፍ አመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን ከአለም አቀፉ የክትባቶች ጥምረት ጋቪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር ጋር በጤና ስርዓቶች ዙሪያ አጋርነታቸዉን ማጠናከር በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጥምረቱ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ለረጅም ጊዜ ላደረገው ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልፀዉ ክትባቱ የሀገሪቱን የጤና ስትራቴጂ ማዕከል ያደረገና በሰው ሃብት ልማት ዘርፍ ወሳኝ ድርሻ እንዳለዉ አመላክተዋል፡፡