በጃፓን ቶኪዮ የግማሽ ማራቶን አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸነፈ

AMN ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም

በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል፡፡ ።

አትሌት ሰለሞን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1:01.21 ወስዶበታል። በሴቶች ምድብ አትሌት መስከረም ማም ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በሌላ ዜና በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል ። በሴቶች ውድድር አትሌት አይናለም ደስታ በ2 :17.37 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን አስመዝግባ አሸንፋለች።

አትሌት ብርቱካን ወልዴ 2ኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ አትሌት መቅደስ ሽመለስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ፈፅማለች። በወንዶች የባለፈው ዓመት አሸናፊ አትሌት ጸጋዬ ጌታቸው 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

አትሌት ጌታነህ ሞላ 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ጨርሰዋል ። የኬንያዊውን አትሌት ጂዮፍሪ ኪብቹምባ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review