ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በአባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈት እጅግ አዝኛለዉ ብለዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ እጅግ ትሁት ፣ የሀገር ወዳድ ምልክት ፣ በሁሉም ዘንድ የሚወደዱ ፣ የሚደመጡ እና የሚከበሩ አባታችን ነበሩ ።
ለቤተሰቦቻቸዉ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ ፣ እንዲሁም ለመላዉ የኢትዮዽያ ሕዝብ በከተማ አስተዳደራችን ስም ልባዊ መፅናናትን እመኛለዉ ብለዋል።