በሩብ ዓመቱ የህዝብ ጥያቄን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና ውይይት ተጠናቋል። በዝግጀት ይባክን የነበር ጊዜን ወደ ተግባር በማስገባት በሩብ ዓመቱ የህዝብ ጥያቄን ሞላሽ መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች መፈፀም መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።
ፈጠራ እና ፍጥነት ለተመዘገቡ ስኬቶች መሰረት መሆናቸውን የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የኑሮ ጫናን ማቃላል ፣ የገበያ ቍጥጥር ማድረግ እና አማራጭ ምርት እንዲቀረቡ ተደርጓል።
በተጨማም አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ፥ በአረንጓዴ ልማት ፣ በፅዳትና ጐርፍ መከላከልን ትኩረት ተደርጐ በመሠራቱ ውጤት ተመዝግቧል ። በእውቀት የታነፀ ትውልድ ለመንንበት በ ትምህርት ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ቀጣይም በብዙ የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል።
ወጣቶች በአምሮም በአካልም ብቁ እንደሆኑ ፣ ህፃናት ቦርቀውና ተጫውተው እንዲያድጉ ፣ ታለንታቸዉን እንዲያሳድጉ መጫወቻና መሰልጠኛ የስፓርት ማዘውተሪያዎች ተገንብተዋል። የሴቶችን ማህበራዊ ተጋላጭነት ለመቅረፍም በነገዋ የክህሎትና ስብዕና መገንቢያ ማዕከል ሴቶችን በማስልጠን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉንና አሁንም ተጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

ቀን ብቻ የሞተሰራ ከተማ ሳትሆን አዲሰ አበባ በምሸትም የምትሰራ ከተማም የማድረግ ሥራ ለውጥ እያስመዘገበ ነው ። አገልግሎት አስጣጥን ለማሻሻል ውጤታማ የሆነ ሥራዎች የተሰሩ ቢሆንም፣ አሁንም አመራሩ ይበልጡን ትኩረት ሰጥቶ ኃላፊነት ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል።
በተቋም መካከል የአፈፃፀም ልዩነቶች በዋናነት የሚፈጠሩት ከአመራር ብቃት እና ስንፍና ጋር የሚያያዙ በመሆኑ ለተሻለ ለውጥ ያለ እረፋት 24/7 የሚሰራ ፥ አገልጋይ አመራር መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል ። በከተማችን የመሰረተ ልማት ጥያቄ አዳጊ ትክክለኛ መሆኑን የገለፁት ከንቲባ አዳናች አቤቤ በቀጣይም አጠቃላይ ሥራዎቻችን በቅደም ተከተል በእቅድ የሚመሩ ይሆናል ብለዋል።
በቀጣይም የከተማችንን ሠላም ከህዝባችን ጋር ማረጋገጥ ፥ የቤት አቅርበትን ማሳደግ፥ አገልግሎትን ለማሻሻል መሶብ የእንድ ማዕከል ዲጅታል አግልግሎት መገንባትና በሰዉ ሃይልና በቴክኖሎጂ ብቁ ማድረግ ፥ የኑሮ ውድነትን ማቃላል የሚያስችሉ ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ፥ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር፥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ማሳደግ ፥ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ማጠናከር፥ የትራንስፖርት ሰርዓቱን ማዘመን ፣ በኮሪደር የለሙ መሰረተ ልማቶች ህዝብ እንዲጠቀምባቸው በአግባቡ ማስተዳደር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማልከታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡