‎መንግስት የግል ኢንቨስትመንት ተሳትፎን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው

You are currently viewing ‎መንግስት የግል ኢንቨስትመንት ተሳትፎን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው

AMN – ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

መንግስት እያደገ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የግል ኢንቨስትመንት ተሳትፎን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ገለፁ።

በአቶ አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጅት ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ እንዲሁም ከባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ዋስትና ኤጀንሲ ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሂሮሺ ማታኖ ጋር ተወያይቷል።

ውይይቱ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።

በዚህም ወቅት በኢትዮጵያ የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ከተቋማቱ ጋር ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር የሚያስችል ምክክር ተደርጓል።

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማፋጠን በሚደረገው ጉልህ እርምጃ ውስጥ ስትራቴጂያዊ ትብብርን ከማሳደግ አንፃር ውይይቱ ጉልህ ሚና እንዳለው አቶ አህመድ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ይህ አጋርነት በኢንቨስትመንቶች ላይ የሚከሰቱ ውስንነቶችን ለመቀነስ ፣ካፒታልን ለማሰባሰብ እና የግሉ ዘርፍ እድገት በኢትዮጵያ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ያለዉን ተሳትፎ ይበልጥ ለማላቅም እንዲሁ።

አቶ አህመድ ሺዴ አክለውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለባለሀብቶች ይበልጥ የተረጋጋና ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው ፣ የሪፎርም ሂደቱን እድገት ለማስቀጠል ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ያለው ትብብር ወሳኝ ነው።

በተለይም በኢነርጂው ዘርፍ የታዳሽ ሃይል ልማት ላይ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት ኢትዮጵያ የሃይል ምንጮቿን አቅም ለማሳደግ ያላትን ፍላጎት፣የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እና በሌሎችም ዘርፎች በትኩረት እየተሰሩ የሚገኙ የኢኮኖሚ አውታሮችን መደገፍ አስፈላጊመሆኑን አስረድተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review