በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ተመራጭ እንዳደረጓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የ44ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የወንዝ ዳር እና ወንዞች ልማት ምልከታ የተደረገ ሲሆን፣የልማት ስራው በጎብኚዎች ዘንድ አድናቆት ተችሮታል።
አዲስ አበባ ከተማ እያደረገች ያለው የልማት ስራ አስደናቂ መሆኑን የገለጹት ጎብኚዎቹ፤ አካባቢን እና እራስን ምቹ እና ጽዱ ማድረግ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ነው ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ተበክለው የነበሩ ወንዞች እና ለመኖር አስቸጋሪ የነበሩ አካባቢዎች ንጹሕ እና ውብ ሆነው መመልከታቸውን የጠቆሙት የሀይማኖት አባቶቹ፣ አዲስ አበባ እንደ ስሟ አዲስ እየሆነች መሆኗንም ገልጸዋል።
የተከናወኑትን የልማት ስራዎች በእኔነት ስሜት መጠበቅ እና መንከባከብ ነዋሪውን ጨምሮ የሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነት መሆኑንም አሳስበዋል።
በሀብታሙ ሙለታ