የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሰላምንና ሰውነትን የሚያስቀድሙ አርአያ አባት ነበሩ

You are currently viewing የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሰላምንና ሰውነትን የሚያስቀድሙ አርአያ አባት ነበሩ

‎AMN ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሰላምንና ሰውነትን የሚያስቀድሙ እንደነበሩ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ገለፁ።

‎የተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ የአስክሬን ሽኝት ስነ-ስርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

‎በአስክሬን ሽኝት መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደተናገሩት፣ በተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር ኢድሪስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው፣ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር ትልቅ ጉድለት ደርሶብናል ብለዋል።

‎የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከመምራት በተጨማሪ፣ መስራች ሆነው እንዳገለገሉም ተናግረዋል።

‎ለሰላም ፣ለአንድነት እና ለህብረት ሁሌም ከፊት የሚቆሙ ፣የሚመሩ ፣የሚቀድሙ እንደነበሩ የገለፁት ዋና ፀሀፊው፤ ከሁሉም በላይ ሰውነትን የሚያስቀድሙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሰው ልጅ ሁሉ ሊከበር የሚገባው ፍጡር መሆኑን፤ ሰውነት ይቅደም፤ ሰውነት ከዘርም ከሀይማኖትም ይልቃል በሚለው ንግግራቸው በብዙሀኑ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ የዘመኑ ጥቅስ ተደርጎ የሚወሰድ እና ከህልፈታቸው በኃላ የሚታወሱበት ድንቅ ንግግራቸው መሆኑንም አስረድተዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review