የመንግስት ሰራተኛውን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥቅማ ጥቅሞች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

You are currently viewing የመንግስት ሰራተኛውን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥቅማ ጥቅሞች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

AMN- ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

የመንግስት ሰራተኛውን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥቅማ ጥቅሞች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ገለፁ።

ለአገልግሎት ፈላጊው ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ስለመሆኑም ኃላፊው ገልፀዋል።

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ በአንድ ዓመት ሁለት ጊዜ የደመወዝ ማስተካከያ መደረጉን ያነሱት ጀማሉ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ከተማም ለመንግስት ሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ለመንግስት ሰራተኛው የሚደረጉ ጥቅማ ጥቅሞች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ከተማ በተለይ በህፃናት አስተዳደግ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥታ በመስራቷ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ ሆናለች፣ የየካ ክፍለ ከተማም በትጋት እየሰራበት ነው ያሉት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣ በክፍለ ከተማው ለህፃናትና ወላጆች ምቹ አካባቢን መፍጠርን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

ክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የመንግስት ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል።

የክፍለ ከተማው የመንግስት ሰራኞች በበኩላቸው፣ መንግስት ለሰራተኛው እየሰራ ያለው ስራ አገልግሎቱ ላይ ያሉ ችግሮችን የሚቀርፍና ለሰራተኞች የሰጠው እውቅናም በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነቃቃ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በፂዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review