AMN ጥቅምት 10/2018 ዓ.
በሁለቱ የባሌ ዞኖች በግብርናው ዘርፍ የተሰራው ስራ ለመላው ኢትዮጰያ የሚተርፍ ምርት የሚገኝበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አማካሪ
አምባሳደር ግርማ ብሩ ገልፀዋል።
የሶፍ ኡመር ወግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በስራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በውቡ ሶፍ ኡመር ዋሻ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ግርማ ብሩ እንደተናገሩት፣ በሁለቱ የባሌ ዞኖች ብቻ 1ሚሊዮን ሄክታር መሬት መታረሱ ገልፀው፣ ምርታማ የሆነው 20 በመቶ እንኳ ቢሆን 20 ሚሊዮን ኩንታል የሚያስገኝ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ ምርት ደግሞ ለመላው ኢትዮጵያ የሚተርፍ መሆኑን አስረድተው፣ ይህንን አከባቢ ነበር ተዘንግቶ የቆየው ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።
እኔ ባሌን የማውቀው የባሌ ጠቅላይ ግዛት በሚባልበት ወቅት ነው ያሉት አምባሳደሩ ፣ በባለፉት ቀናት በሁለቱ የባሌ ዞኖች በግብርናው ዘርፍ የተሰራው ስራ ለመላው ኢትዮጰያ የሚተርፍ ምርት የሚገኝበት መሆኑን ነው ።
በሔለን ተስፋዬ