ህብረተሰቡ በሀብት ላይ ተቀምጦ በድህነት መኖሩ ያስቆጫል፦ አባ ዱላ ገመዳ

You are currently viewing ህብረተሰቡ በሀብት ላይ ተቀምጦ በድህነት መኖሩ ያስቆጫል፦ አባ ዱላ ገመዳ

AMN- ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞ እና በስራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በሶፍ ኡመር ዋሻ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የቀድሞው የመንግስት ባለስልጣን አባ ዱላ ገመዳ ፣ ባሌ ሁሉም ነገር ያለበት፣ ለሁሉም የሚበቃ ሀብት የሚገኝበት አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል ።

ባሌን ለብዙ አመታት እንደሚያውቋት የተናገሩት አባ ዱላ፣ አሁን ባዩዋት ደረጃ ግን እንደማያውቁት ገልጸዋል።

አክለውም ህብረተሰቡ በሀብት ላይ ተቀምጦ በድህነት መኖሩ ያስቆጫል ብለዋል አቶ አባ ዱላ።

እንዲህ አይነት ሀብት በሚገኝበት አካባቢ የሚኖረው ህብረተሰብ መሰረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት እና በድህነት የሚኖር መሆኑ እንደሚያስቆጭም አንስተዋል።

የአካባቢው ወጣት ይህን የመሰለ ፀጋ እያለው ከመጠቀም ይልቅ ወደ ወጪ ሀገር በመሰደድ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖርም አመላክተዋል።

በተጨማሪም ሀገሪቱ በርካታ ሃብቶች እያሏት አልምተን ከመጠቀም ይልቅ ወደ አልተፈለገ ጭቅጭቅና ንትርክ ወስጥ መግባታችን ተገቢነት የለውም ሲሉ ጠቁመዋል ።

ኢትዮጵያ አቅም፣ እውቀትና ጉልበት ያለዉ ወጣት የሚገኝባት ሀገር በመሆንዋ፣ አሁን የተጀመረውን ሀብት በማልማት ከድህነት መላቀቅ ይኖርብናል ሲሉም በቁጭት ተናግረዋል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review