የቱሪስት መስህቦችን ከመልክዓ ምድር በላይ የታሪክ እና የባህል ትስስርን ለማጠናከር ማዋል እንደሚገባ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

You are currently viewing የቱሪስት መስህቦችን ከመልክዓ ምድር በላይ የታሪክ እና የባህል ትስስርን ለማጠናከር ማዋል እንደሚገባ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ

AMN- ጥቅምት 10/2018 ዓ/ም

የቱሪስት መስህቦችን ከመልክዓ ምድር በላይ የታሪክ እና የባህል ትስስርን ለማጠናከር ማዋል እንደሚገባ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

”የሶፍ ዑመር ወግ” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀድሞና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ እንዳሉት የቱሪስት መስህቦችን በዚህ መልኩ መጎብኘታችን ሀገሪቱ ያላትን ፀጋዎች ለማወቅና ለመጠቀም እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

የሶፍ ዑመር ዋሻም ሆነ የባሌ ተራራ በመልክዓ ምድሩ ከመኩራት ባለፈ ታሪኩን አልተረዳንም ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ጉብኝቱ ታሪኩ የኛም ነው ብሎ ለመቀበል እድል ፈጥሯል ብለዋል።

ይህም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ግንኙነት በመልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን በታሪክ፣ በባህል፣ በፖለቲካና በመተባበር ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን ለመፍጠር እድልን ያሰፋል ነው ያሉት።

ከ13 አመት በፊት ሶፍ ዑመርን እንደጎበኙ አቶ ጌታቸው ገልፀው፤ መልክዓ ምድሩ እንጂ ሀብትነቱ እና ታሪኩ አልታየኝም ነበር ብለዋል።

አሁን ላይ ያየነውና የተረዳነው ሀገሪቱ ያላትን ሀብት፣ አኗኗር እና የአየር ሁኔታን በመጠቀም ህዝቡን እንዴት የልማቱ ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል በሚል ቁጭት ለመስራት መነሳሳትን ይፈጥራል ብለዋል።

ይህን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ዜጎች ከሴፍቲኔት ወጥተው እጃቸው ላይ ያለውን ሀብት በመጠቀም ከራሳቸው አልፎ ለሌላ መትረፍ እንደሚችሉም አመላካች መሆኑን አንስተዋል ።

የባሌን የተፈጥሮ ፀጋዎችን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ሀብቶችን ከቱሪዝም መስህብ በተጨማሪ በምግብ ራስን ለመቻል እንዲሁም ለየት ያለ የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማምጣት አቅም ይፈጥራል ብለዋል ፡፡

በ-በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review