ባሌ ብዙ ሃገሮች በአንድ ላይ ያላቸውን መስህብ ብቻዋን ጠቅልላ የያዘች የኢትዮጵያ ምድር ነች ሲሉ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገለጹ

You are currently viewing ባሌ ብዙ ሃገሮች በአንድ ላይ ያላቸውን መስህብ ብቻዋን ጠቅልላ የያዘች የኢትዮጵያ ምድር ነች ሲሉ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገለጹ

AMN – ጥቅምት 10/2018 ዓ. ም.

ኢትዮጵያ ከድህነቷ ለመውጣት ብሎም ለማደግ እና ህዝቧን ለማበልጸግ ፈጣሪ ሁሉንም ሃብቶች አሟልቶ የሰጣት ሀገር መሆኗን አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለምን ማደግ አቃታት? ለምንስ አልተለወጥንም በማለት ጥያቄ የፈጠረባቸውን ጉዳይ በማንሳት ሀገራችን ማደግ የነበረባት ዛሬ ሳይሆን ትላንት ነበር ይህም ከአሁኑ ትውልድ በፊት ነበር ሲሉ አንስተዋል።

አምባሳደሯ አክለውም የእስከዛሬ አለማደግ ያለፈው ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ አለማሰብ፣ ለመጪው ትውልድ ዋጋ ከፍሎ፣ ለትውልድ የተሻለች ሀገር አውርሶ ለማለፍ የሚተጋ ካለመኖሩ የተነሣ ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል ።

ኢትዮጵያ ሁሉም የማደግ መብቶች የተሰጣት ሀገር እንደሆነች አምባሳደር ናሲሴ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጥሩ ማሳያ ሊሆን የሚችለው የባሌ ዉብ የተፈጥሮ ጸጋዎች መሆናቸውን እና ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለባሌ እንዲነግሯቸው ሲጠየቁ ባሌን ለመግለጽ ከባድ ይሆንባቸው እንደሆነ በቃላት ከመስማት በላይ በአካል ተገኝተው እንዲመለከቱ ይጋበዙ እንደነበርም አውስተው ይህንን እውነታ ዛሬ በአካል ተገኝተው ማረጋገጣቸውን ነው የተናገሩት ።

አምባሳደሯ በቆይታቸው እንዳስተዋሉት፣ ባሌ ሁሉም የማደግ እድሎች የተሰጣት መሆኗን በመግለጽ ፣ ባሌ ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ የመላ ኢትዮጵያ የዳቦ ቅርጫት ማድረግ የሚያስችላት ምቹ መልክዓ ምድር እና አቅም እንዲሁም የተፈጥሮ ጸጋ አላት ሲሉ ነው የገለፁት።

ከባሌ የሚነሱና ገባር ወንዞች ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ፣ጎረቤት ሀገራትንም ተሻግሮ ከሰላሳ ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብን ውሀ የሚያጠጡ ወንዞች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በአካባቢው በዚች ጥቂት አመታት ውስጥ በተጀመሩ ስራዎች በጣም ትላልቅ ለውጦች የታየበት መሆኑን የገለፁት አማባሳደሯ፤ በዚህም ድንቅ የአመራር ጥበብና ችሎታም የታየበት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በግብርና፣ በቱሪዝም እና በሌሎቹም የልማት ዘርፎች ላይ በመሰማራት፣ ህዝባችንን በመለወጥ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሃገር ለማስረከብ አሻራችንን አስቀምጠን ማለፍ አለብን ነው ያሉት አምባሳደሯ።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review