የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከAfrica 50’s ዋና ስራ አስፈጻሚ አላይን ኢቦቢሴ ጋር በዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ባላቸው የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ውይይታቸው በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ከሚገኘው እኤአ የ2015 የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።
በዚህ ወቅት አቶ አህመድ ሽዴ የመሰረተ ልማት ግንባታ የሀገሪቱ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑንና ሀብትን ዘርፈ ብዙ ትርጉም ባላቸው ፕሮጀክቶች ላይ ለማዋል መሰረታዊ ፍላጎት እንደሆነም ነው ያነሱት።
ፈጠራ እና ለመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚሆን ፋይናንስ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ያለውን ሰፊ ፍላጎት ለማሟላት እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
የAfrica 50’s ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢቦቢሴ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ቀጣናዊ ትስስሩን ሊያፋጥኑ በሚችሉ እጅግ ጠዋሚ በሆኑ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ከኢትዮጵየ መንግስት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ማረጋገጣቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።
አፍሪካ 50 የአፍሪካ ሀገራት ዕድገታቸውን ሊያፋጥኑ በሚችሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የሚያደርግ አህጉራዊ ተቋም ነው።