ሴቶች ሰላምን በማስፈን ረገድ እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing ሴቶች ሰላምን በማስፈን ረገድ እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

AMN – ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም

ሴቶች ሰላምን በማስፈን ረገድ እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀለፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን ለትውልድ ግንባታ ላይ ከሴቶች የሚጠበቁ ሚናዎችን በማስመልከት ከከተማው ከተወጣጡ ሴቶች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ሴቶች ሰላም በማስፈን ረገድ እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የከተማዋን ሰላም አስተማማኝ እና ዘላቂ በማድረግ ረገድ የሴቶች ሚና የማይተካ እንደነበር በማስታወስ፣ ይህንኑ ተግባራቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን ለማጎልበት የሚያግዝ ጥናታዊ ፅሁፍ በመድረኩ ቀርቧል።

ጥናታዊ ፅሁፉን መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሃሳቦች እና አስተያይቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

መድረኩ በቀጣይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review