መገንጠልም መጠቅለልም አይሰራም

You are currently viewing መገንጠልም መጠቅለልም አይሰራም
  • Post category:ፖለቲካ

AMN- ጥቅምት 11/2018 ዓ. ም

መገንጠልም መጠቅለልም አይሰራም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ከቀድሞ እና በስራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር በተዋበው ሶፍ ዑመር ዋሻ ”የሶፍ ዑመር ወግ” በሚል ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም፤ ልጠቅልል የሚለውም፣ ልገንጠል የሚለውም ኢትዮጵያን አላወቃትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መገንጠልም መጠቅለልም አይሰራም፤ የሚቻለው በመስማማት፣ በትብብር ሁሉም ያለውን ሃብት እያወጣ እንዲለማ አድርጎ መኖር ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ይህንን መገንዘብ አለመቻል ነው ችግር ያማጣብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ልገንጠልም ልጠቅልልም በሚል የሚንቀሳቀስ ፓርቲም ሆነ ሌላ አካል ሃገሩን፣ ህዝቡን እና ባህሉንም አያውቅም ነው ያሉት፡፡

ስለሆነም ያለው ምርጫ ተከባብሮ፣ ተደማምጦ፣ ተጋግዞ እና ተካፍሎ በጋራ መኖር እንደሆነ በማመን ነው፣ ይህ ሲሆን ሰላማችን እና ልማታችን ይመጣል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review