ኢትዮጵያን በ48 ኪሎ ግራም የወከለችው ቦክሰኛ ፈጣን ቢጆ የታንዛኒያዋን ተጋጣሚ በማሸነፍ ለፍጻሜ አልፋለች፡፡ቡጢኛዋ ለወርቅ ሜዳሊያ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ተወዳዳሪ ጋር ትፋለማለች፡፡
6 ቦክስኞችን ወደ ኬኒያ የላከችው ኢትጵያ እስከ አሁን 2 ነሃስና አንድ ብር ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በምስራቅ አፍሪካ ውድድር ኢትዮጵያ ነገ ተጨማሪ 2 ውድድሮች ታደርጋለች፡፡በ54 ኪሎ ሴት ሮማን አሰፋ በ57 ኪሎ ወንድ ደግሞ ፍትዊ ጥኡማይ ውድድሮቻቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ሻምፒዮናው የፊታችን አርብ ፍጻሜውን ያደርጋል፡፡
በዮናስ ሞላ