ኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ልማት ፈንድ በቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ያላቸውን አጋርነት እንደሚያጠናከሩ አስታወቁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና የሳዑዲ ልማት ፈንድ በቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ ያላቸውን አጋርነት እንደሚያጠናከሩ አስታወቁ

AMN- ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በ2025 የዓለም ባንክ እና የአይኤምኤፍ አመታዊ ስብሰባዎች ላይ ከሳዑዲ ልማት ፈንድ (ኤስኤፍዲ) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱልጣን አብዱራህማን አል ማርሻድ ጋር ተወያይተዋል።

ስብሰባው በኢትዮጵያ እና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ያለውን ጠንካራ የልማት አጋርነት አጉልቶ አሳይቷል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ኤስ ኤፍ ዲ ለኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴ እያደረገ ላለው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ግቦችን ለማሳካትም ትብብርን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አዲሱን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሜጋ ፕሮጀክትን ጨምሮ ኢትዮጵያ በኃይል እና በቁልፍ የመሠረተ ልማት ዘርፎች ላይ ያላትን የኢንቨስትመንት ፍላጎት በአፅንዖት ገልጸዋል።

የኤስኤፍዲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱልጣን አብዱራህማን አል ማርሻድ፣ የሀገሪቱን ዘላቂ የልማት ግቦች ለሚደግፉ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ፈንዱ ለአዲሱ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ አዳዲስ የትብብር ዘርፎችን ለማካተት ፈቃደኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህም የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያበረታታ፣ የስራ እድል የሚፈጥር እና ማህበራዊ ደህንነትን የሚያሻሽል መሆኑን ጠቁመዋል።

ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በሳዑዲ አረቢያ መካከል የግሉ ሴክተር ተሳትፎን ለማሳደግ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነቶችን ለማጠናከር በሚረዱ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review