ኢትዮጵያ እና ሩስያ የቆየ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸዉን የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር በሞስኮ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ እና ሩስያን የቆየ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያም ሀሳብ መለዋወጣቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።