አርሰናል ሦስተኛ ተከታታይ የቻምፒየንስ ሊግ ድሉን አሳካ

You are currently viewing አርሰናል ሦስተኛ ተከታታይ የቻምፒየንስ ሊግ ድሉን አሳካ

AMN-ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም

በኤምሬትስ አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው አርሰናል በድንቅ ብቃት 4ለ0 አሸንፏል።

በሁለተኛው አጋማሽ የተቆጠሩትን አራት ግቦች ቪክቶር ዮኬሬሽ(ሁለት) ፣ ጋብርኤል ማጋሌሽ እና ጋብሬኤል ማርቲኔሊ ከመረብ አሳርፈዋል።

አርሰናል ያደረጋቸውን ሦስት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በሙሉ ማሸነፍ ችሏል።

በሦስቱ ጨዋታዎች ስምንት ግብ አስቆጥሮ አንድም ግብ አልተቆጠረበትም።

በሌሎች ጨዋታዎች የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ፓሪሰን ዠርማ ባየር ሊቨርኩሰንን 7ለ2 ረቷል።

በሜዳው የጆዜ ሞሪንሆን ቤኔፊካ ያስተናገደው ኒውካስትል 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

የሴሪአው ሻምፒዮን ናፖሊ በኔዘርላንዱ ክለብ ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን አስደንጋጭ የ6ለ2 ሽንፈት ደርሶበታል።

ማንችስተር ሲቲ ቪያሪያልን 2ለ0 ፣ ኢንተር ሚላን ኡኑዮን ሴንት ጂልዋስን 4ለ0 ማሸነፍ ችለዋል። ወደ ዴንማርክ ያቀናው ቦሩሲያ ዶርትመንድ ኮፐንሀገን ላይ የ4ለ2 ድል አስመዝግቧል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review