አንዴ ብቻ የሚያገባው የፓሮት ዝርያ

You are currently viewing አንዴ ብቻ የሚያገባው የፓሮት ዝርያ

AMN- ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም

‎”አንድ ሰው ለአንድ” የሚለው ብሂል ለፓሮት የአዕዋፍ ዝርያ አባባሉም፣ ምሳሌውም የሚገባቸው ይመስላል። በአማዞን ጫካ የሚርመሰመሰው የፓሮት ዝርያ፣ በኢትዮጵያም በአንድ ወጣት ቤት ከትሟል። ወጣት የኑስ መሱድ “እኔስ በሀገሬ እንኳን ሰው ወፍ አለምዳለሁ” የሚለውን የሀገሬውን ሰው አባባል እየኖረው ይገኛል።

‎ወጣቱ ከኤ ኤም ኤን አዲስ መዝናኛ ጋር በነበረው ቆይታ፣ ስካርሌት ማካዋ የተሰኘ የፓሮት ዝርያ በእድሜ ዘመኑ አንዴ እንደሚያገባ ተናግሯል። ‎ስካርሌት ማካዋ ጥንዶች ከሆኑ የሚፈለፈሉትን ፓሮቶች ሴቷ እና ወንዱ በጋራ የሚንከባከቡ ሲሆን፣ ወንዱም በአግባቡ ሀላፊነቱን እንደሚወጣና ታማኝነቱን ያስረዳል።

‎ከሁለቱ አንዳቸው በህይወት ከሌሉ በድጋሚ ሌላ ጥንድ የማይፈልጉ ናቸው ሲል አስገራሚ ባህሪያቸውንም ተናግሯል። እነዚህ የአእዋፍት ዝርያዎች በአማካይ 80 ዓመታት በምድር ላይ እንደሚኖሩ ወጣት የኑስ ገልጿል። ሰባት አይነት ስካርሌት ማካዋ የተሰኙ የአእዋፋ ዝርያዎች መኖራቸውን የሚገልፀው ወጣቱ፣ አንዱ ዝርያ ከእርሱ ጋር መኖሩን እና ሌሎች ደግሞ በአማዞን አካባቢ የሚገኙ ናቸው ብሏል።

‎አንድን ፓሮት ለማሰልጠን ብቻውን መሆን እንዳለበት ገልፆ፣ የብዙዎች ጥያቄ ግን አጋር እንዲመጣለት ነው፡፡ ሆኖም ግን አጋር ካገኙ ከሰዎች ጋር ያላቸው ቅርርብ እንደሚቀንስ ተናግሯል። ፓሮት በባህሪው ከሰዎች ጋር ከሚቀራረቡ የአእዋፋት ዝርያዎች አንዱ ሲሆን ከአዋቂዎች ይልቅ ከህፃናት ጋር ቃላትን የመናገር ሁኔታዎቹ ይልቃል።

‎እነዚህ የአእዋፋት ዝርያዎች ከሌሎች የሚለያቸው ረዥም እድሜ ስለሚኖሩ ነው ብሏል። ወጣቱ ያልተለመዱ የአእዋፋት ዝርያዎችን በቤቱ ያረባል። ይህ ለብዙዎች ቀልብ የሚስብ ተግባር ቢሆንም ለእርሱ ደግሞ የሰርክ ተግባሩ ነው ።

‎ወጣት የኑስ በመኖሪያ ቤቱ የተለዩ የአእዋፍ ዝርያዎችን ማርባት ከጀመረ ስምንት አመታትን አስቆጥሯል። የኑስ በመኖሪያ መንደሩ ፓሮት፣ ቦሃራ ትራንፒተር፣ እርግብ እና ሌሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን ያተረፉ የአእዋፋ ዝርያዎችን እያረባ ይገኛል።

‎አንዳንዶቹ አእዋፋት ውበት ያላቸው በመሆናቸው በዓለም አቀፍ መድረክ በተለይም ‘’ቦሀራ ትራንፒተር’’ የተሰኘውን የአእዋፍ ዝርያ የማወዳደር ሀሳብ እንዳለው አስረድቷል። ሳድል ፋንቴል የተሰኘ የአእዋፍ ዝርያም በግቢው ከሚያረባቸው ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

‎እነዚህ ሁሉ የአእዋፋት ዝርያዎች በወጣቱ ቤት የተራቡ ሲሆኑ፣ ወላጆቻቸው ከውጭ በማምጣት የተጀመረ ስራ መሆኑን ነው የገለፀው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአእዋፋት ዝርያ “ጃኮቢን” የተሰኘው የአእዋፍ ዝርያ ፋሽን ከሆኑ ወይም ተዋዳጅነትን ያተረፉ መሆናቸውን ወጣቱ ተናግሯል።

‎ከዚህ በተጨማሪ አውስትራሊያ ሎሪኪት የተሰኙ የአእዋፋት ዝርያዎች ጭምር በግቢ ውስጥ የሚያረባው ወጣቱ፤ ሪንግኔክ፣ ቶራኮ የተሰኙ ዝርያዎች ተናግረዋል። ቶራክ የተሰኙት የወፍ ዝርያ ሆነው የፖሮት ዝርያ ያልሆኑ ሲሆኑ ከእነዚህ ውጭ ያሉት በኢትዮጵያ በአንዳንድ አከባቢዎች የሚገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል።

‎የአእዋፋቱ ዝርያዎች ባህሪያቸው የተለያዩ መሆናቸውን የጠቆመው ወጣቱ፣ ለአብነትም የአውስትራሊያ ሎሬኬቶች በመጠኑ ንዴታም መሆናቸውን ተናግሯል። የቶራኮ ዝርያዎች ደግሞ ከዛፍ ወደ ዛፍ የመዝለል ባህሪ እንዳላቸው ገልጿል።

በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review