በ2017 ዓ.ም ከ 16 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንዲዉል ተደርጓል

You are currently viewing በ2017 ዓ.ም ከ 16 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንዲዉል ተደርጓል

AMN – ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም

በ2017 ዓ.ም ከ 16 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንዲዉል መደረጉ ተገለፀ፡፡

በከተማችን በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የተሳተፉ ልበ ቀናዎችን ስለ መልካም ተግባራቸዉ በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በመላዉ የከተማችን ነዋሪዎች የየእለት ተግባር እና ባህል እየሆነ በመጣው የበጎነት ተግባር ያዘመሙ ቤቶች ተቃንተዋል ፣ የአገር ባለዉለታዎች ፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸዉ ፣ ለከፋ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር የተጋለጡ በርካታ ወገኖቻችንን በመርዳት የኑሮ ጫናቸዉ እንዲቃለል ተደርጓል ፣ በአካባቢ ጥበቃ ፣ አረንጔዴ አሻራ ፣ የደም ልገሳ ፣ የትራፊክ ደህንነት አገልግሎትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች አመቱን ሙሉ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እየተሳተፉ ይገኛል ።

አዲስ አበባ ባለፉት 7 የለዉጥ አመታት ወጣቶቿን ፣ ባለሀብቶቿን ፣ መላዉ ነዋሪዎቿን ፣ የተለያዩ የሙያ ዘርፍ ባለቤቶችን በማስተባበር አመቱን ሙሉ በዘለቀ የበጎ ፈቃድ ተግባር ዉስጥ በማሳተፍ ከ 42 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት በበጎ ፈቃድ ተግባር በማሰባሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት ተችሏል ።

በ2017 ዓ.ም እንዲሁ ከ 16 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንዲዉል ተደርጓል። ከዚህ ዉስጥ 2.2 ቢሊዮን ብር አስተዋፅኦ በማድረግ የዘንድሮዉንም ልዩ ሽልማት የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ጉሩፕ ወስዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምድርም በሰማይም ዋጋዉ ከፍ ባለ መልካም ተግባር ዉስጥ በተለያየ መንገድ ያለ ስስት አሻራችሁውን ላኖሩ፣ መስጠት ላላጎደለባቸዉ ልበ ቀና የከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review