የሃገራችን መጻኢ ተስፋ የሚለመልመዉ በሰላም መንገድ ስንጓዝና ነፍጥ ያነሱ ሀይሎችም ወደ ሰላም ሲመጡ ብቻ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠየቁ፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ የ2018 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ አመታዊ ስብሰባን ማካሄድ ጀምራለች፡፡
በጉባኤዉ መክፈቻ ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በአገራችን የሚታየዉ አለመረጋጋት ቤተ ክርስቲያንዋም ላይ ጫና መፍጠሩን አዉስተዉ፤ የእርስ በርስ ግጭቱ ተወግዶ ችግርንም በንግግር መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ሲኖዶሱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡
የአገራችን መጻኢ ተስፋም የሚለመልመዉ በሰላም መንገድ ስንጓዝ ብቻ መሆኑን በመግለፅ፤ ነፍጥ ያነሱ ሀይሎችም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ ፓትርያርኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ጉባኤው ለአገር ሰላም ጾሎት ከማድረግ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ ለሚነሱ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳቦችና ዉሳኔዎች ይተላለፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በየሺዋስ ዋለ