3 ሺህ 240 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

You are currently viewing 3 ሺህ 240 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

AMN- ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 240 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 2745 ወንዶች፣ 479 ሴቶች እና 16 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 210 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ተግልጿል።

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ባለው ያላሰለሰ ጥረት እስካሁን 22 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review