የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት አካሂዷል።
ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሶስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፡-

1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ ምክር ቤት አባላትን ቁጥር ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ በመወያየት ለምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል።
2ኛ. የተቋራጭ የግንባታ ግዢና የሥራ ስምሪት የአሰራር ደንብ ቁጥር ……. /2018 ላይ ተወያይቶ ወሳኔ አሳልፏል፡፡
3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች የመሬት ጥያቄ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ማሳለፉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡