ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለአፍሪካውያን በራስ አቅም የይቻላል መንፈስን ማረጋገጥ እንደሚቻል መሠረት የጣለ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ገለፁ፡፡
46ኛው ጉሚ በለል የውይይት መድረክ “የህዳሴ ግድብ ድል ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ በመገኘት ውይይቱን ያስጀመሩት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በጋራ ዋጋ ከፍለው ያገኙት ድል ነው ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካውያን በራስ አቅም የይቻላል መንፈስን ማረጋገጥ እንደሚቻል መሠረት የጣለ ነው ብለዋል።
በቀጣይ በታላቁ ህዳሴ ግድብ የታየውን የጋራ ህብረት በሌሎችም የልማት ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
2018 ዓመት፣ ፕሮጀክቶች ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚሸጋገሩበት፣ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ፍሰት የሚያድግበት፣ ትላልቅ ስኬቶች የምንጎናፀፍበት ነው ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ፤ የህዳሴ ግድብን እውን ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን በጋራ የሰሩት ገድል ነው ብለዋል። ይህም የኢትዮጵያን ከፍታ ያመላከተ የጋራ ድል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሀመድኑር ዓሊ