የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በማህበራዊ ክላስተር ስር የተደራጁ አስፈጻሚ ተቋማት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በማህበራዊ ክላስተር ስር የተደራጁ አስፈጻሚ ተቋማት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራረሙ

AMN ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና በማህበራዊ ክላስተር ስር የተደራጁ አስፈጻሚ ተቋማት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸዉን የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡

ማህበራዊ ክላስተሩ የተለያዩ ተቋማትን በአንድ ያሰባሰበ ሲሆን ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የማህበራዊ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከተቋማቱ አመራሮች ጋር የፊርማ ስነስርአቱን አካሂደዋል።

የትምህርት ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ፣ አካታች ማህበራዊ ጥበቃን ማስፈን፣ ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ማብቃት የማህበራዊ ክላስተሩ ከሚሰራቸው ተግባራት መካከል ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፣የጤና ቢሮ ፣ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የምገባ ኤጀንሲ፣ የባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ፣ አብርሆት ቤተመጽሀፍ እና የስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ጽ/ቤት የክላስተሩ አባላት ናቸው።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review