ሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ነፃ ለማድረግ የተጀመረው ኢንሼቲቭ በዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝቷል።
ዕውቅናው የተሰጠው ከኪዩቢክ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ነፃ ለማድረግ በተጀመረው የተቀናጀ አሠራር ለተገኘው ውጤት መሆኑን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ተናግረዋል።
ዕውቅናው ከመሰጠቱ በፊት ሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ቆሻሻ የፀዳች በማድረግ ያገለገሉ የፕላስቲክ ቁስን ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል አስቻይ ሁኔታ እንዳለ መገምገሙንም ጠቁመዋል።
ኢኒሼቲቩ ለሴቶች እና ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩም በግምገማው መነሳቱን ነው አቶ ሔኖክ የተናገሩት።
የሐረር ከተማን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ነፃ ለማድረግ እና የፕላስቲክ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም በዝቅተኛ ዋጋ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት በኪዩቢክ ኢትዮጵያ እና ሐረር ከተማ መካከል በፈረንጆቹ ሚያዝያ 2024 ስምምነት መፈረሙን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የተጀመሩ ሥራዎች በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።