የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመንና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመፍጠር በ2018 በጀት አመት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡

You are currently viewing የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመንና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመፍጠር በ2018 በጀት አመት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡

AMN- ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን በስሩ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሚሰጡን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመንና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመፍጠር በ2018 በጀት አመት ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዷል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተንኩዌይ ጆክ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፣ በበጀት አመቱ ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም፣ ገቢው የሚሰበሰበው ተጠሪ የልማት ድርጅቶች ከሆኑት ከቄራዎች ድርጅት፣ ከኤግዚብሽን ማዕከል፣ ከህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር፣ ከንግድ ስራዎች፣ ከሲኒማ ድርጅቶች፣ ከኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት እና ከሌሎችም ድርጅቶች እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ይህን ለማሳካትም የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ ምቹ የስራ ቦታና ተቋማዊ ቅንጅታዊ አሰራር እየተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ የ2018 በጀት አመት 1ኛው ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምና ክትትል ድጋፍ ሪፖርት ከተጠሪ ተቋማት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

በፋሲል ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review