ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ አበክሮ እንደሚሰራ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስምረት አስታወቀ

You are currently viewing ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ አበክሮ እንደሚሰራ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስምረት አስታወቀ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN -ጥቅምት 14/ 2018 ዓ/ም

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስምረት ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ አበክሮ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስምረት የመስረታ ጉባኤዉን አካሄዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የፓርቲው መስራች አባል የአሆኑት አቶ ጌታቸዉ ረዳ ፤ የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ አቶ መለስ አለሙ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የፓርቲው አባላት ተሳትፈዋል።

ፓርቲው ሃገራዊ ጥቅሞችና ስትራቴጂክ የልማት እቅዶች እንዲሳኩ ከተለያዩ ፓርቲዎችና የፖለቲካ ሃይላት ጋር እንደሚሰራ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አቶ ብርሃነ ገብረኢየሱስ ተናግረዋል፡፡

በሃገራችን የተጀመሩ ትላልቅ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችና የባህር በር ጥያቄ ግቡን እንዲመታ በሃገራዊ አጀንዳ ላይ መግባባት አለብን ብለዋል፡፡

በተለይም በዚህ ጊዜ በትጥቅ ትግል የሚመጣ ለውጥ ስለሌለ የትጥቅ ትግል አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ወደ ሰላም መምጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

የፓርቲዉ ማእከል የትግራይ ክልል ነው ያሉት አቶ ብርሃነ፣ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች ሃገራዊ ፓርቲዎች ጋር በመነጋገር በልማትና ሃገራዊ አጀንዳዎች ተሳትፎቸውን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

በምሩጽ ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review