የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል

You are currently viewing የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል
  • Post category:ቱርዝም

AMN – ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም

የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት የጎንደር ከተማን ወደ ሕይወት መልሷቷል ሲሉ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የታሪካዊ ሥነ-ሕንፃዎች ጥበቃ እና እድሳት የሥነ-ሕንፃ እሴቶችን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ታላቅ የኢትዮጵያ ቤተ-መንግሥት የነበረው የጎንደር አብያተ መንግሥት በሚያምር እና የመነሻውን አርክቴክቸር በጠበቀ መልኩ ውብ ሆኖ መታደሱን ም ገልጸዋል።

አሁን ጎንደር ድሮ እና ዘንድሮን አጣምራ የያዘች ማራኪ እና የምታምር ከተማ መሆኗን ነው ፕሬዚዳንቱ የጠቀሱት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review