የደም ማነስ መንስኤ ምንድነዉ? ምልከቱና መከላከያውስ?

You are currently viewing የደም ማነስ መንስኤ ምንድነዉ? ምልከቱና መከላከያውስ?
  • Post category:ጤና

AMN- ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

ደም ማነስ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የጤና ችግር ነው።

ደም የሰው ልጅ የህይወት መሰረት ሲሆን፣ ደም ይሰጣል፣ ደም ይወሰዳል፣ ደም ይቀጥናል፣ ይወፍራል፣ ያንሳል እንዲሁም ይበዛል።

በየካቲት 12 መታሰቢያ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጠቅላላ ሀኪም ዶ/ር አቢዮት አለሙ፣ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የደም ማነስ ምልክቶች የቆዳ መገርጣት፣ የራስ ማዞርና ከፍተኛ የድካም ስሜት መሆናቸውን አንስተዋል።

ደም ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ ነጭ የደም ሴል፣ ፕላትሌት እና ቀይ የደም ሴል በመባል እንደሚለዩ ገልጸዋል።

ነጭ የደም ሴል በሽታን ለመከላከል፣ ፕላትሌት ደም ሲፈስ ለመዝጋት እና ቀዩ የደም ሴል ደግሞ ኦክስጅንን የማጓጓዝ ስራ እንደሚያከናውኑ ባለሙያው አብራርተዋል።

ደም ማነስ የሚከሰትበት ምክንያት ሄሞግሎቢን ግራም በተለያዩ ምክንያቶች ጤና ሲያጣ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አቢዮት፣ የልኬት መጠን በዴሲ ሊትር ከ13 እስከ 17 ከሆነ ጤናማ መሆኑን ገልፀው፣ ከዚህ ከበለጠ ወይም ካነስ የጤና ችገር መኖሩን ያረጋግጣል ብለዋል።

ደም ማነስ የበለጠ የሚያጠቃቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት እና በእርግዝና ወቅት ያሉ እናቶችን እንደሆነ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ዶክተር አቢዮት አስረድተዋል።

ለዚህም ምክንያቱ የብረት ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ መሳሳት መሆኑን ጠቅሰው፣ በእርግዝና ላይ ያሉ እናቶች የተመጠጣነ ምግብ በመመገብ በቂ የጤና ክትትል ከማድረግ በተማጨሪ ደም በመቀበል የኑሮ ሁኔታን ማሻሻል በደም ውስጥ የሚገኘውን ሄሞግሎቢን ጤናማነትና መጠን በመጨመር ደም ማነስን መከላከል እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከ7 ዴሲ ሊትር በታች የሆነ ደም ማነስ ከባድ ችግር ውስጥ በመሆኑ አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ አመጋገብን በማስተካከል ዘላቂ የጤና መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል ዶ/ር አቢዮት አስገንዝበዋል።

በአለኽኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review