ኢትዮጵያ በየ 100 ቀናቱ እየተቀየረች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ በየ 100 ቀናቱ እየተቀየረች ነው

AMN- ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በየ 100 ቀናቱ እየተቀየረች እና እያደገች ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 ዓ.ም የ100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር አድርገዋል።

በውይይቱ ሰዎች እነሱ ከሄዱ የኢትዮጵያ ነገር ያበቃለት ከዕድገት ጉዞዋ የምትቆም ይመስላቸዋል ያሉት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ኢትዮጵያ ግን እያደገች ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከእኔ ውጪ አይሆንላትም ብሎ አኩርፎ የሄደ ሰው እድገቷን የማየት ዕድል ይቀርበታል፣ ያጣዋል እንጂ የኢትዮጵያ እድገት አይቆምም ሲሉም ነው የገለጹት።

አኩርፎ ከሄደም ደግሞ ቶሎ ቢመጣ ጥሩ ነው ያሉት አማካሪ ሚኒስትሩ፣ ካልሆነ ብዙ ነገሮች ተቀይረው፣ አልፈው፣ ብዙ ታሪኮች ይሰራሉ ያንን ታሪክ ለማወቅ እስኪደርስም ሀገር የዕድገት ጉዞ ላይ ነች በማለትም አክለዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review