የምግባረ ሰናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ማስፋፊያ ተጠናቆ ተመረቀ

You are currently viewing የምግባረ ሰናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ማስፋፊያ ተጠናቆ ተመረቀ

AMN- ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚተዳደረው ምግባረ ሰናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ማስፋፊያ ተጠናቆ ተመርቋል፡፡

በሆስፒታሉ የማስፋፊያ ምርቃት ብፁዓን አባቶች የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል ።

የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢው ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለሆስፒታሉ መመረቅ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዉ ለዚህም ስኬት ባለድርሻ አካላትን እናመሰግናለን ብለዋል።

የሆስፒታሉ አገልግሎቱ ዘመናዊ እና ለተገልጋይ ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተሰራ ስለመሆኑ አከለዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቀሲስ ኢንጂነር ሱራፌል ተዘራ በበኩላቸው ሆስፒታሉ በቀን ከ400 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከ60 በላይ የአልጋ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በቅርቡም በ8 የኩላሊት ዲያሊሲስ ማሽኖች አገልግሎት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

11ወራትን የፈጀው የምግባረ ሰናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጎበታል ።

በወንድማገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review