በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሃግብር በሜዳ ኤምሬትስ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው አርሰናል 1ለ0 አሸንፏል።
የቀድሞ ክለቡን የገጠመው ኤብሪቼ ኤዜ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
እንግሊዛዊው የአጥቂ አማካይ በሊጉ ለአርሰናል ግብ ሲያስቆጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ድሉን ተከትሎ ሰባት ተከታታይ የሊግ ጨዋታ ያሸነፉት መድፈኞቹ ነጥባቸውን 22 በማድረስ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ተሸንፏል።
በቪላ ፓርክ አስቶንቪላን የገጠመው ሲቲ 1ለ0 ተረቷል። የቪላን ግብ ማቲ ካሽ ማስቆጠር ችሏል።
ቦርንማውዝ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2ለ0 በማሸነፍ በ18 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ወልቭስ ከ በርንሌይ ያደረጉት ጨዋታ በበርንሌይ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በሸዋንግዛው ግርማ