ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ2ኛዉ ምዕራፍ ተጀምረዉ በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ በከተማችን በ 2ኛዉ ምዕራፍ ተጀምረዉ በተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ለ አራቱ ማለትም (1) ከመስቀል አደባባይ መገናኛ – ሳዉዝ ጌት፣ (2) ከአንበሳ ጋራዥ -ጎሮ ፣ (3) ከአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል ፣ ጎሮ ፣ቦሌ ቪ አይ ፒ ተርሚናል እንዲሁም ከሳር ቤት -ጀርመን አደባባይ ፣ጋርመንት ፉሪ አደባባይ ኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ አካላትን አመስግነናል ብለዋል።
በዚህም በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት ሌት እና ቀን ሲሰሩ ለነበሩ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪዎች ፣ማህበራት ፣በጎ ፈቃደኞች እና ሌሎችም ለነበራቸዉ ከፍተኛ አስተዋፆ እና ትዉልድ ተሻጋሪ ስራ አመስግነናል ።

በተለይም መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች ለሚነዙ ሀሰተኛ አሉባልታዎች ጆሮ ሳይሰጥ የልማት ተነሺ ሆኑትም ያልሆኑትም ለጋራ ልማት በመተባበር ፣ ቡና እያፈላ ፣ ዉሃ እያቀረበ ለልማት ስራዉ ዉጤታማነት ላሳየዉ ከፍተኛ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለዉ ።
በ 1ኛ እና በ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተጠናቀቁ መሰረተ ልማቶች መካከል 342 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ፣ 185 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ ፣241 ኪ.ሜ የሳይክል መንገድ ፣ ዘመናዊ የመንገድ መብራቶች ፣ በርካታ የህዝብ መገልገያ እና መዝናኛ ቦታዎች ፣ በርካታ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶች ፣ 101 የህፃናት መጫወቻዎች ፣ 155 የስፓርት ማዘዉተሪያዎች ፣ 153 ዘመናዊ ፓርኪንግ እና ተርሚናሎች እንዲሁም 210 የሕዝብ መፀዳጃዎች ተገንብተዉ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ሲሉ ገልጸዋል።