በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሩዋንዳ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሩዋንዳ

AMN – ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በኢትዮጵያ የተጀመረዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ የአፍሪካ ሃገራት ተሞክሮዉን በመጋራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ኬንያ ተሞክሮውን በመውሰድ፣ ከ2 ሳምንታት በፊት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩን ማስጀመሯ የሚታወስ ሲሆን፣ ሩዋንዳም የኬኒያን ፈለግ በመከተል፣ በትናንትናው እለት መርሃ ግብሩን በይፋ መቀላቀሏን ከሩዋንዳ የደን ሚኒስቴር ማህበራዊ የትሥሥር ገጽ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የሩዋንዳ የደን ባለስልጣን መስሪያ ቤት፤ በዚህ አመት ዘመቻ ከ65 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በመላ ሀገሪቱ እንደሚተከሉ ይፋ አድርጓል።

ዘመቻው “ችግኞችን እተክላለሁ፤ ተንከባክቤ አጸድቃለሁ፤ በዚህም ምድርን እታደጋለሁ” በሚል መሪ ቃል ተጀምሯል።

ይህ ተነሳሽነት ማህበረሰባዊ ግንኙነቶችን የሚያጠናክር እና ወጣቶችን ለልማት የሚያነሳሳ ከመሆኑም በተጨማሪ፤ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚከሰተው ችግርም እፎይታን እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ በተገበረችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፤ 47 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ስኬት ማስመዝገቧ ይታወሳል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review