መላው የሰው ዘር ዓድዋን ሲያስብ ነጻነትን እና ድልን ያስባል ሲሉ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing መላው የሰው ዘር ዓድዋን ሲያስብ ነጻነትን እና ድልን ያስባል ሲሉ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ጥቅምት 17/2018

ደራሲ፣ የሃይማኖት ምሁር እና የሥነ ፈለክ ባለሙያ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

መላው የሰው ዘር ዓድዋን ሲያስብ ነጻነትን እና ድልን ያስባል ያሉት መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) በዓድዋ ድል መታሰቢያ በነበራቸው ቆይታ እንደተደሰቱ ገልፀዋል፡፡

የዓድዋ አርበኞች ነጻነታችንን ለማስጠበቅ ደማቸውን አፍሰዋል፤ አጥንታቸውን ከስክሰዋል፤ ለነሱ መታሰቢያ እንዲሆን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዚህ መልኩ መገንባቱ አስደስቶኛል ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡

የሥነ ፈለክ ባለሙያው መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ፤ በነበራቸው ጉብኝት ዛሬ ላይ ሆኜ ትላንትን ማየት ችያለሁ ያሉ ሲሆን ዓድዋ በአፍሪካዊያን ልብ ውስጥ ታትሞ የሚቀመጥ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ስር የሌለው ግንድ፤ ግንድ ያልተሸከመው ቅርንጫፍ የለም፤ ስሮቻችን ቅድመ አያቶቻችን ናቸው፤ ግንዱ እኛ ነን፤ ቅርንጫፎቻችን ከኛ የሚገኙ የልጅ ልጆች ናቸው፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ላይ ቆሜ ወደ ኋላ እንዳስብ አድርጎኛል ማለታዉቸዉን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review