በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጠጥን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጠጥን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

AMN ጥቅምት 17/2018

በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጠጥን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የ5ቱን ተጠሪ ተቋማት፣የክፍለ ከተሞች እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መዋቅሮችን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ህይዎት ጋር የተገናኘው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሆኑ የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ የማብራት አገልግሎት፣የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት፣የእሳት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽንና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማትን የሶስት ወራት አፈጻጸም ተገምግሟል።

ባለፉት ሶስት ወራት የክረምት ወቅት እንደነበረና በከተማ ደረጃ ታላላቅ ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት መስተናገዳቸውን የጠቀሱት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ እነዚህንም ለማሳካት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ሲሰጡ መቆየታቸውንም ገልጸዋል።

ተቋማቱ ከኮርደር ልማት ጋር ተያይዞ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ተቀናጅቶ በመሥራትም በሩብ ዓመቱ አበረታች ተግበራትን ከተማዋን በሚያዘምን መልኩ ማከናወናቸው ተጠቅሷል።

በሩብ ዓመቱ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎች የከተማዋን ዕድገት የሚመጥኑ መሆናቸውን የጠቀሱት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተቋማት ቅንጅታዊ ሥራዎችም በሲቪል ምዝገባ፣በሃይል አቅርቦት፣በከተማ ጽዳትና በአደጋ ስጋት መከላከል የተሠጡ አገልግሎቶች ስኬታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሁለተኛ ሩብ ዓመትም ተቋማትን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልጌሎት ለመሥጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር እና የተቋማት መጠናከር ላይም በትኩረት እንደሚሠራም ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review