ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ለማግኘት ታንዛኒያን ይገጥማሉ

You are currently viewing ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ለማግኘት ታንዛኒያን ይገጥማሉ

AMN-ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

ለ2026ቱ የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታውን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ይጠብቀዋል።

በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከታንዛኒያ ጋር የተደለደሉት ሉሲዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከቀናት በፊት በዳሬሰላም አከናውነው 2ለ0 መሸነፋቸው ይታወሳል።

የመልሱ ጨዋታ ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ የሚከናወን ይሆናል።

በስብስቡ በመጀመሪያው ጨዋታ ያልነበሩት አምበሏ ሎዛ አበራ እና አርአያት ኦዶንግ ተካተዋል።

ትናንት በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ የድሬዳዋ ሕዝብ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ሎዛ አበራ በበኩሏ አሸንፈው ወደ አፍሪካ መድረክ ለመመለስ መዘጋጀታቸውን ገልፃለች።

ብሔራዊ ቡድኑ ውጥቱን ቀልብሶ ካለፈ ከ14 ዓመት በኋላ ወደ መድረኩ ይመለሳል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፈው እ ኤ አ በ2012 ኢኳቶሪያል ጊኒ ባሰናዳችው ውድድር ላይ ነበር።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review