በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ ከተሰሩ ስራዎች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬታማ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ ከተሰሩ ስራዎች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬታማ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN – ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ ከተሰሩ ስራዎች መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ስኬታማ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በ2017 የተከናወኑ አበይት ጉዳዮችን ዳሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ 2017 ዓ.ም በርካታ ጉዳዮችን ያሳካች ሲሆን በህዝብ ተሳትፎ ከተተገበሩ ተግባራት መካከል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትልቁ ስኬት የተገኘበት ሲሆን በዚህም 25 ሚሊዮን ዜጎች በየ ዓመቱ ሳይታክቱ ባደረጉት ተሳትፎ እና መንግስት ህዝብ ባደረጉት የተቀናጀ ስራ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል በዓለም ትልቁ ስኬት መሆን ችሏል ብለዋል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ ቅንጅትን በተግባር ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በፍሬህይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review