በኢትዮጵያና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው አጋርነት ዘላቂ ልማትና ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ገለጹ።
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ለ2025 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ ግብር የ90 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር ተፈራርመውታል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት ለ2025 ዓመታዊ የድርጊት መርሃ ግብር የ90 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናንስ ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል።
ስምምነቱ እንደ መሬት አስተዳደር፣ የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የአየር ንብረት መቋቋም፣ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት እና ከስደት ተመላሾች ድጋፍ ባሉ አራት ቁልፍ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚያተኩር ጠቅሰዋል።
ይህም በአዲስ የትብብር መንፈስ ለረጅም ጊዜ የቆየውን ትብብር የሚያጠናክር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል።
ስምምነቱ በኢትዮጵያና በአውሮፓ ኅብረት መካከል ያለው አጋርነት ዘላቂ ልማትና ብልፅግናን ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን መናገራቸዉን ተዘግቧል፡፡