አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትምህርት ዘርፉ ላበረከተው አስተዋፅኦ በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ተሸላሚ ሆነ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትምህርት ዘርፉ ላበረከተው አስተዋፅኦ በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ተሸላሚ ሆነ

AMN – ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትምህርት ዘርፉ ላበረከተው አስተዋፅኦ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በአዲሱ የAMN PLUS የቴሌቭዥን ቻናሉ የቴሌቪዥን ትምህርት ዝግጅቶችን ይዞ መቅረብ ከጀመረ ሰንብቷል፡፡

ጣቢያው የቴሌቪዥን ትምህርት ዝግጅቶችን ከ4ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ፣ የሂሳብ ትምህርት በአማርኛ ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ሳምንቱን ሙሉ ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ”የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራት” በሚል መርህ በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ500 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅና መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡

በዘርፉ አስተዋጽኦ ያደረጉ ተቋማትም እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም በዕውቀት የተገነባ ትውልድ ለመፍጠር ባደረገው አስተዋፅኦ በከተማ አስተዳደሩ ልዩ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

በሚካኤል ሂሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review