AMN ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በተሰሩ የኮሪድርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ወጣቶችን ከሱስ እና ከአልባሌ ቦታ አውጥተን የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
የኮሪደር ልማቱ የቤተሰብ ጊዜንና የጋራ መዝናኛን በማህበረሰቡ ዘንድ ማሳደጉን እና ባህል ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ወጣቶችን ከአልባሌ ስፍራና ቦታ ተሻምተን ወስደናቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ወጣቶችንና ማህበረሰቡን ከጫት ቤት፤ ከድራፍት ቤትና ከሌሎች ሱሶች አውጥተን ጊዚያቸውን በስፖርዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያሳልፉ ማድረግ ችለናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኮሪደር ልማቱ አማካኝነት ለወጣቶች የተፈጠሩ መዝናኛና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ለሀገሪቱ የወደፊት የስፖርት ስኬት አስተዋፅኦ እንዳለውም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በብሔራዊ ቡድን መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾች ከ10 ዓመት በኋላ እንደሚያፈሩ ም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተናገሩት ።
በሔለን ተስፋዬ