ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ማድረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደዉ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸዉን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንዲከታተሉም አስታዉቋል፡፡
ተማሪዎች የተመደቡበተን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
1. Website: https://student.ethernet.edu.et
2. Telegram bot: @moestudentbot መሆናቸዉን ትምህርት ሚኒስቴር ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡